ከ6 ሺሕ 400 በላይ መዝገቦች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ

Date:

በተለያዩ ተቋማት የሚያገለግሉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ‘በደል ደርሶብናል’ በሚል ከከፈቷቸው ከ7 ሺሕ በላይ መዝገቦች መካከል ከ6 ሺሕ 400 በላይ መዝገቦች እልባት ማግኘታቸውን የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአሐዱ አስታውቋል።

በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ላይ ሠራተኞች ‘በደል ደርሶብና’ ብለው መዝገብ የከፈቱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ለአሐዱ በላከው መረጃ አመላክቷል።

ይሁን እንጂ በ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7 ሺሕ 457 የሚሆኑ መዝገቦች የተከፈቱ መሆናቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል ከ1 ሺሕ 100 በላይ የሚሆኑት ካለፈው ዓመት የተሻገሩ መሆኑንም አያይዞ ገልጿል።

እንዲሁም እልባት ከገኙት መዛግብት መካከል ከ3 ሺሕ 800 በላይ የሚሆኑት የተዘጉ ሲሆን፤ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ውሳኔ ያገኙ መሆናቸውን በመረጃው አብራርቷል።

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተለይ ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ፣ የግልፅ ችሎት ቁጥርን የመጨመር፣ የቴክኖሎጂ መር አገልግሎትን የመስጠት፣ ለተገልጋዮች የአንድ መስኮት አገልግሎትን በማሳለጥ እንዲሁም የተሻለ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

እንዲሁም የሥራ ክርክር ችሎት ሲታዩ ከነበሩት መዛግብት ውስጥ ከ1 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በቀጠሮ መተላለፋቸውን አንስቷል።

በዚህም ከለፈው ዓመት ማለትም ከ2016 ዓ.ም. ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አፈጻጸም የተገኘ መሆኑን የጠቆመው መረጃው፤ ለቀጣይ የተሻለ እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት በእቅድ እየተሰራ መሆኑንም አመላክቷል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...