በመዲናዋ  102 የምሽት ጭፈራ ቤቶች ታሽገዋል

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን  በተደጋጋሚ የአካባቢ ብክለት በሚያደርሱ 3 ሺህ 249 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ፤ የከተማዋን የአካባቢ ብክለት፤ የድምፅና የፍሳሽ ብክለት ከተሽከርካሪ የሚለቀቀውን ጭስ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

የአካባቢ ህግ መከበርን ለማሣደግ 13 ሺህ 4 መቶ 85 አገልግሎት ሰጪና አምራች ተቋማትን ለመቆጣጠር መታቀዱን ጠቅሰው፤ 14 ሺህ 8 መቶ 72 ተቋማት ላይ የቁጥጥርና ክትትል ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በዚህም ከድምጽ ብክለት ጋር  በተያያዘ በመዲናዋ 102 ጭፈራ ቤቶች ከአንድ እና ከሁለት ማስጠንቀቂያ በኋላ በአግባቡ ማስተካከያ ባለማድረጋቸው እንደታሸገባቸው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በህግ ማስከበር ሒደቱ ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ ከቅጣት እንዳገኘም  አስታውቋል፡፡

በተደጋጋሚ የአካባቢ ብክለት በሚያደርሱ 3 ሺህ 2 መቶ 49 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ያሉት አቶ ዲዳ፤ 3 ሺህ 66 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውና 183 ተቋማት መታሸጋቸውን ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ዜጎቿ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ አዳዲስ ወታደራዊ ጥቃቶች ሊሰነዘሩ...

ፍትህ ተሰውቶ የጉልበት ብልጫ የገነነበት ውሳኔ ነው

ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ስርዓት መመሪያ (Financial...

“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች” የተባሉ ግለሰቦች በምክክሩ እንዲሳተፉ በምን መስፈረት ተመረጡ?

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 17ኛ ቀን ውሎ የክልል ተወካዮች ጉባኤ...

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...