መንግስት በጥድፊያ የሚጀመሩና በመሠረተ ድንጋይ ደረጃ የሚቀሩ ግንባታዎች እንዲኖሩ አይፈቅድም

Date:


የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ መርሃግብር  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ዛሬ በስካይት ላይት ሆቴል ይፋ ሆኗል።

በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ ዘርፉ በርካታ ውስብስብ #ችግሮች ያሉበት ነው ብለዋል።

የግንባታ የጥራት ጉድለት፣ የግብዓት እጥረትና ሙስና  ከችግሮቹ መካከል እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

ዛሬ ይፋ የሆነው ኢኒሼቲቭ እነዚህን ችግሮች በማስቀረት ዘርፉን ውጤታማ ያደርጋል የሚል እምነት መንግስት እንዳለውም ተናግረዋል።

ቁልፍ የሚባሉ የዘርፉን ተዋናዮች በማሳተፍ የተዘጋጀ ኢኒሼቲቭ እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሣኒ ናቸው።

ለሚቀጥሉት ሃያ አምስት ዓመታት እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከውጪ የሚገቡ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ መተካትን፣ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን እንዲሁም በሠው ሃይል ስልጠና፣ ስምሪትና ምዘና ዙሪያ አዳዲስ አሰራሮችን ማስተዋወቅን ታሳቢ ያደረገ ኢኒሼቲቭ ነውም ብለዋል።

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ለጥቅል አገራዊ ምርት ወይም #GDP ሃያ በመቶ ድርሻ እንደሚያበረክት ተነግሯል ።

አምራች ዜጋ ከሆነው ሃይል ለአስር በመቶው የስራ ዕድል የፈጠረ ነውም ተብሏል።

ከ35,000 በላይ ኩባንያዎች ተሠማርተው የሚገኙበት ዘርፍ እንደሆነም በመርሃ ግብሩ ላይ ሲነገር ሠምተናል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...