ግብፅ በአባይ ወንዝ ያላትን መብት አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች

Date:


የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በአባይ ወንዝ ላይ የሚደረጉ ማንኛውንም የአንድ-ወገን እርምጃዎችን ውድቅ በማድረግ ግብፅ የውኃ ሀብት መብቷን ችላ ትላለች ብሎ የሚያምን ማንኛውም ሰው «ተሳስቷል» ሲሉ አስጠንቅቀዋል።


ሲሲ ከዩጋንዳ አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በካይሮ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት ወደ ነጭ እና ጥቁር  አባይ የሚፈሱ ገባር ወንዞች ዓመታዊ የውኃ ፍሰት 1,600 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ፤ አብዛኛው በደን፣ ረግረጋማ አካባቢ፣ በትነት እና በከርሰ ምድር ውኃ ይጠፋል።


«ከአባይ ወንዝ ድርሻችን ትንሽ የውኃ ክፍል ብቻ ሲሆን ግብፅ እና ሱዳን በአንድ ላይ 85 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ያገኛሉ፤ ይህም ከጠቅላላው 4 በመቶው ብቻ ነው» ብለዋል ።


የግብፅ መሪ አገሪቷ አማራጭ የውኃ ሀብት ስለሌላት እና አነስተኛ ዝናብ ስለምታገኝ ይህንን የውኃ ድርሻ መተው «የግብፅን ሕይወት መተው ማለት ነው» ሲሉ አሳስበዋል።


ሲሲ ግብፅ የናይል ውኃ ለእህት ሃገራት  በግብርና፣ በኤሌክትሪክ ወይም በአጠቃላይ  የሚያበረክተውን የልማት ፋይዳ የምትቀበል ቢሆንም  «እንዲህ ያለው እድገት ግብፅ የሚደርሰውን የውኃ መጠን መቀነስ የለበትም» ብለዋል።


ኢትዮጵያ ባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ በመስከረም ወር በይፋ እንደሚመረቅ አስታውቃለች።
በጎርጎሪያኑ 2011 ዓ.ም.ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፤ የውኃ ፍሰት መቀነስ በአባይ ወንዝ ላይ ያለውን ድርሻ ሊጎዳ ይችላል በሚል ስጋት ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የዲፕሎማሲያዊ ውጥረት መነሻ ሆኖ ቆይቷል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...