ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት ምርቶቿን ከቀረጥ ነጻ በሆነ ሥርዓት ወደ አፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ማዕቀፍ አባል አገራት መላክ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጡት መግለጫ ፤ ኢትዮጵያ መስከረም 29 ቀን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የሸቀጦች ንግድ ትግበራን በይፋ ታስጀምራለች።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዋና ስራ አስፈጻሚን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙም ተጠቁሟል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ የምትልከው እንደ በቆሎ እና ቦለቄ ያሉ ሸቀጦች 15 በመቶ ቀረጥ ይጣልባቸው እንደነበር ነው። ነገር ግን፣ የመጀመሪያውን ጭነት ካስጀመረች በኋላ፣ ኢትዮጵያ ወደ ኬኒያ የምትልከው ሸቀጥ ከቀረጥ ነጻ እንደሚሆን ተናግረዋል።
CapitalNews
