በኢትዮጵያ በቤተሰብ ስም የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው አርሶ አደሮች ቁጥር ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ከ67% ወደ 74% ቢያድግም፣ ይህ ህጋዊ መሻሻል በተግባር ግን የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ማምጣት አለመቻሉ ተገለጸ።
ካፒታል ባገኘዉ አዲስ መረጃ መሠረት፣ በመሬት ባለቤትነት ላይ የወንዶች ቁጥጥር ከነበረበት 27% በከፍተኛ ደረጃ ወደ 45% ከፍ ብሏል። ይህ የሚያሳየው መሬት በህጋዊ መንገድ ሲረጋገጥም እንኳ ቁጥጥሩ ወደ ወንዶች እየተዛወረ መሆኑን ነው ተብሏል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI ግኝት እንዳመለከተዉ ግኝቶች ሴቶች በአማካይ በቀን 20 ሰዓት ሲሰሩ፣ ወንዶች ደግሞ 14 ሰዓት ብቻ ይሰራል ይላል።
ይሁን እንጂ ሴቶች በግብርና ውሳኔ አሰጣጥ እና በአስፈላጊ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች ተደራሽነት ላይ ዝቅተኛ ተሳትፎ እንዳላቸዉ የተገለፀ ሲሆን የጥናቱ ተመራማሪዎቹ ማህበራዊ ደንቦች የሴቶችን ተሳትፎ የሚገድቡ ዋነኛ መሰናክሎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
እስከ 2025 ዓ.ም. ድረስ 30% የሚሆኑ ቤተሰቦች ሦስቱን ቁልፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች (የተሻሻለ ዘር፣ ማዳበሪያ ወይም አግሮ-ኬሚካል) አንዱንም አልተጠቀሙም።
እንደ ጥናቱ ከሆነ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን ያገኙ ቤተሰቦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል (ከ1,186 ወደ 926)። ይህ ደግሞ የድጋፍ ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ የአገልግሎት አሰጣጥ ሞዴሎች ዘላቂነት የጎደላቸው መሆናቸውን ያመለክታል።
CapitalNews
