አሜሪካ በቬንዙዌላ የባህር ዳርቻ ዕፅ አዘዋዋሪ ጀልባ ላይ በወሰደችው እርምጃ 4 ሰዎች መግደሏን አሳወቀች።
የአሜሪካ ጦር ትላንት አርብ በቬኔዙዌላ የባህር ዳርቻ ላይ ወደ አሜሪካ አደንዛዥ እፅ ሲታጓጉዝ የነበረ ጀልባን መምታቱን የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት ተናግረዋል።
በእርምጃው አራት ”ናርኮ” የተሰኙ የአሸባሪ ቡድን አባላት መገደላቸውን የፔንታጎን ዋና አዛዥ ተናግረዋል።
በካሪቢያን አካባቢ አደንዛዥ ዕፅ ያዘዋውራሉ በተባሉ መርከቦች ላይ የሚደረገው ዘመቻ ፥ ፕሬዝደንት ትረምፕ የህግ አውጭዎች ይፋዊ ማስታወሻ ላይ አሜሪካ አሁን ከአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች ጋር ጦርነት ውስጥ መሆኗን እና ከአዘዋዋሪዎቹ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ህገወጦች መሆናቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
በዚህም አሜሪካ አደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎችን ያለመ የጥቃት ዘመቻ የቀጠለች ሲሆን፥ ከሳምንታት በፊትም የአሜሪካ ኤፍ-35 ስውር ተዋጊ ጀቶች በቬኔዙዌላ የአደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ቡድን ሰፈሮች ላይ ከባድ ጥቃት መፈጸማቸው ይታወሳል።
