የኦክስጅን ተደራሽነትን በማሻሻል ሞትን መቀነስ ይገባል

Date:

የህክምና ኦክስጅን አቅርቦትና ተደራሽነትን በማሻሻል ሞትን መቀነስ የሚገባ መሆኑን የጤና ሚንስቴር ገለጸ። በሀገሪቱ ያሉ የኦክስጅን ማምረቻዎችን ከሦስት ወደ 58 ማሳደግ መቻሉንም የሚንስቴሩ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

“የኦክስጅን ተደራሽነትን በማሻሻል ልንከላከል የምንችለውን ሞት እንቀንሳለን” በሚል መሪ ሃሳብ የዓለም የኦክስጅን ቀን ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተከበረበት ወቅት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ እንደገለጹት፤ የህክምና ኦክስጅን አቅርቦትን ጥራት እና ተደራሽነት በማሻሻል መከላከል ሞትን መቀነስ ይገባል።

የህክምና ኦክስጅንን በተገቢው መንገድ መጠቀም እና ቀጣይነት ያለው የኦክስጅን ሥርአትን ለመገንባት ከባለድርሻ አካላት ብዙ የሚጠበቅ መሆኑንም ሚንስትር ዲኤታዋ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው “የህክምና ኦክስጅን አቅርቦት መሻሻሉ የእናቶችና ህጻናትን ሞትና ስቃይ በመቀነስ ሂደት ከፍተኛ ሚና አለው” ብለዋል።

የህክምና ኦክስጅን በቀዶ ህክምና፣ በጨቅላ ሕፃናት እና በአዋቂዎች ፅኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ደረጀ፤ ይህንን ታሳቢ ያደረገ የኦክስጅን ማምረቻዎች ከነበረበተ 3 ወደ 58 ማሳደግ መቻሉንም ተናግረዋል።

(#አዲስ_ማለዳ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...