በኢትዮጵያ አንድም የፍራፍሬ ጭማቂ ፋብሪካ የለም

Date:

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የፍራፍሬ መጠጦች ደረጃን ይፋ ባደረገበት ወቅት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የፍራፍሬ ጭማቂ ወይም ጁስ የሚያመርት አንድም ፋብሪካ እንደሌለ አስታውቋል፡፡ 

ባለሥልጣኑ በሀገር ውስጥ የሚመረቱት ከአልኮል ነጻ ለስላሳ መጠጦች የፍራፍሬ ቃና ወይም (Fruit Flavor) ብቻ መሆናቸውን ገልጿል።

በባለስልጣኑ የእንስሳት ተዋጽኦና አልሚ ምግብ ዴስክ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሑሴን ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ አንድ የፍራፍሬ ጫማቂ ጁስ ተብሎ እንዲጠራ ቢያንስ የመጠጡ 30 በመቶ የተፈጥሮ ፍራፍሬ ሊካተትበት ይገባል።

የፍራፍሬ ይዘቱ 30 በመቶ በታች ከሆነ የፍራፍሬ ጭማቂ ተብሎ እንደማይጠራ አብራርተዋል፡፡

አቶ መሐመድ ሑሴን በተጨማሪም፤ “በሱፐርማርኬቶች እና በመደብሮች ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የሀገር ውስጥ ምርቶች ጁስ የሚያስብላቸውን መስፈርት አላሟሉም” ብለዋል፡፡

ምርቶቻቸውን ጁስ ወይም የፍራፍሬ ጭማቂ በሚል መጠሪያ ያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች የጁስ ደረጃን ባለማሟላታቸው ሙሉ በሙሉ እንዲታገዱ ተደርጎ፤ “ፍሩት ፍሌቨር ድሪንክ” በማለት እንዲሠሩ መደረጉን ኃላፊው ገልጸዋል።

ባለሥልጣኑ ዜጎች በምርቶቹ አጠራር እንዳይደናገሩና የፍራፍሬ ጭማቂ በሚል ስያሜ ገበያ ላይ የቀረቡት ሁሉ የጁስ ደረጃን የማያሟሉ እና ከ30 በመቶ በላይ የፍራፍሬ ጭማቂ በውስጣቸው የሌለ እንደሆነ ግንዛቤ እንዲወሰድ አሳስቧል፡፡

የፍራፍሬ ቃና (ፍሩት ፍሌቨር) ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የፍራፍሬ መጠጦችም የጁስ መስፈርቱን አሟልተው እንዲገቡ አስፈላጊው ቁጥጥር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...