የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን የያዘ መጽሐፍ ተመረቀ

Date:

ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላትን ይዟል

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ ተመርቋል።

‎በመዝገበ ቃላቱ የመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተነግሯል፡፡

‎በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር በላይ ካሳ  እንዲሁም  ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

‎ዶ/ር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው።

‎ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...