በዓለም ብቸኛዋ በምግብ ራስን መቻል ያረጋገጠች ሀገር

Date:

በቅርቡ “ኔቸር ፉድ” (Nature Food) በተባለው ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ በወጣ ጥናት መሠረት፣ ከ186 ሀገራት መካከል ጋይና (Guyana) የተባለችው የደቡብ አሜሪካ ሀገር ብቻ በሁሉም ዋና ዋና የምግብ አይነቶች ራሷን ችላ መገኘቷ ተገለጸ።

ይህ የጋይና ስኬት፣ የምግብ እጥረትና በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ጥገኝነት እያደገ ባለበት ዘመናዊው ዓለም ውስጥ እውነተኛ የምግብ ነፃነትን የሚያሳይ ብርቅዬ ሞዴል አድርጓታል።

ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ጋይና ሰባቱን ዋና ዋና የምግብ አይነቶች ማለትም ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ዓሳ፣ ሥጋ፣ በእፅዋት ላይ የተመሠረተ ፕሮቲን (ጥራጥሬዎችና ፍሬዎች) እና ስታርች ያላቸው ዋና ዋና ምግቦች በበቂ ሁኔታ አምርታ ሕዝቧን መመገብ ትችላለች።

ይህ ማለትም ሀገሪቱ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ሳትደገፍ ሙሉ ህዝቧን ለመመገብ የሚያስችል የአገር ውስጥ ምርት አላት ማለት ነው።

ብዙ አገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የምግብ ዋስትና እጦትና ዓለም አቀፍ የንግድ መደጋገፍ ችግር እየገጠማቸው ባለበት በዚህ ወቅት፣ ጋይና የላቀ አቋም ያላት ብቸኛዋ ሀገር ሆና ተገኝታለች።

የጋይና ዘላቂነት ያለው የግብርና አሰራር እና ልዩ ልዩ የአገር ውስጥ ምርት መኖሩ፣ ለዚህ ስኬት ዋና ምክንያት ነው ተብሏል።

ይህ ጥናት ጋይናን እንደ እውነተኛ የምግብ ነፃነት አምሳያ በማስቀመጥ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአገር ውስጥ የግብርና አቅምን ማሳደግ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ትልቅ ትምህርት ሰጥቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...