አሜሪካ ለሴት ፕሬዝዳንት ዝግጁ አይደለችም ሲሉ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ተናገሩ

Date:

ባለፈው ምርጫ እንዳየነው በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ዝግጁ አይደለንም ሲሉ ሚሼል ኦባማ ተናግረዋል።

አሜሪካ ሴቶችን አግላይ የሆነ የፖለቲካ ምህዳር ነው ያላት ያሉት ሚሼል፤ አሜሪካውያን ሴትን ለዋይት ሀውስ ለመምረጥ ዝግጁ አይደሉም ሲሉ በ2024 የቀድሞዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን በማሳያነት አንስተዋል።

የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት፤ሁሉም ይዋሻል እውነታው ግን በሴት ለመመራት ዝግጁ አይደለም ብለው፤አሜሪካ ያሉ ወንዶች አንዲት ሴት ስትመራቸው ማየት ምቾች ይሰጣቸዋል ብለዉ እንደማያምኑ አስረድተዋል።

“ታውቃላችሁ፣ እኛ(ሴቶች) ለማደግ ብዙ ማድረግ ያሉብን ነገሮች አሉ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም በሴት መመራት እንደሚችሉ የማይሰማቸው ብዙ ወንዶች አሉ፣ ይህንን እኛም ተመልክተናል”ብለዋል።

ሚሼል ኦባማ ‹‹ዘ ሉክ››በተሰኘዉ በዚህ ዓመት ባሳተሙት መጽሃፋቸው በፋሽን፣ በፀጉር እና በውበት እንዲሁም በዋይት ሀውስ ውስጥ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ቀዳማዊት እመቤት በመሆን ያሳለፉትን ቆይታ የገለፁ ሲሆን፤ ብዙ ጊዜ በፖለቲካ ውስጥ ያሉ ሴቶች የሚዳኙት በመምራት ችሎታቸው ሳይሆን በአካላዊ ቁመናቸው እንደሆነም ጽፈዋል።

ህዳር 08/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...