907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 

Date:



በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ5 ሺህ በላይ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር በመካሄድ ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረጉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አራት ወራት በ5 ሺህ 203 የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ላይ የደረሰኝ ቁጥጥር ማካሄዱን ገልፆል፡፡

የደረሰኝ ቁጥጥሩ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ በሚገቡ፣ከከተማዋ በሚወጡና በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ  የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፣ሚኒባሶችና አነስተኛ ሽፍን መኪኖች ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም ያለደረሰኝ ጭነት በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 907 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 1 ሺህ 39 ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲቆርጡ 997 ግብር ከፋዮች ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው የቁጥጥር የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎቹ የጫኗቸው ሸቀጦች ላይ የ954 ሚሊዮን 803 ሺህ ብር ደረሰኝ እንዲቆረጥባቸው ለማድረግም ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የደረሰኝ ቁጥጥሩ በቀን ብቻም ሳይሆን በለሊት ጭምር ተጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጥ በመጫን በሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ላይ ከሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በቀጣይ የደረቅ ጭነት አሽከርካሪዎቻቸው ላይም የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚደረግ መሆኑ ቢሮዉ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...