ውበቱ የላይቤሪያው ክለብ LSCR አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

Date:

የቀደሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከላይቤሪያው ክለብ ጋር ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡

አሰልጣኙ በሚያስመዘግበው ውጤት እና በጋራ ስምምነት እንደ አስፈላጊነቱ ውሉ ሊራዘም የሚችልበት ዕድል እንዳለ ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡

በ2003 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው ውበቱ አባት ፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በርካታ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን አሰልጥኗል፡፡ በተጨማሪም በሱዳን ሊግ አል አህሊ ሸንዲን ማሰልጠኑ የሚታወስ ነው፡፡

ክለቡ LSCR የበርካታ ልምድ ባለቤት የሆነውን አሰልጣኝ በመቅጠሩ ደስተኛ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የላይቤሪያው ክለብ ቫርማህ ኮፖቶ እና ሞሀመድ ሸሪፍን የአሰልጣኝ ቡድኑ አባለት ሆነው እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በላይቤሪያ ዋናው ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው LSCR ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች 5ቱን ብቻ አሸንፎ በ20 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...