በአፍሪካ ሚዲያ አዋርድ በልዩ ካታጎሪ ሽልማት (Special Category Awards) የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ደረጀ አሸናፊ ሆናለች።
በምርጥ የቪድዮ ፕሮዳክሽን ዘርፍ ከሩዋንዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሂርዋ አይማብሌ አሸናፊ ሲሆን፤ በአፍሪካን ኢንዲፔንደንት ዘርፍ (African Independent Category) ልዩ ዘርፍ ደግሞ ኩዳክዋሼ ሞዮ ከዚምባቡዌ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አሸንፏል።
የአፍሪካን ሰላም፣ ልማት እና ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎች የሽልማቱ አካል ሲሆኑ፣ በፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ የሚታወቁ ግለሰቦችና ተቋማትም በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
