ቲክቶክ በናይጄሪያ የምሽት የቀጥታ ስርጭቶች እንዳይደረጉ አገደ

Date:

የቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ቲክቶክ በናይጄሪያ በምሽት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል።

ቲክቶክ በናይጀሪያ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን ማቆሙን ይፋ ያደረገው ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ስርጭቶች መብዛታቸውን ተከትሎ ነው።

ይህ የወሲብ ይዘት በብዛት ይሰራጭበታል በተባለው በዚህ ሰዓትም በናይጄሪያ የቀጥታ ስርጭቶችን ማሰናዳት ወይም መመልከት አይቻልም።

“የይዘት ደህንነትና ተጠቃሚዎቼን እጠብቃለሁ” ያለው ቲክቶክ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ከ49,000 በላይ የቀጥታ ውይይቶችን ከናይጄሪያ አጥፍቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲክቶክ እውቅና እና ትኩረት ለማግኘት በሚል ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ማሰራጨት እየተለመደ ሲሆን ቲክቶክ በተደጋጋሚ ቁጥጥር እንዲያደርግ በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ ቆይቷል።

ቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ያሳወቀው ነገር የለም።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...