የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሩቶ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በማህበራዊ መገናኛ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጉብኝቱ « በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው» ብለዋል።
በተጨማሪም በሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪቃ ቀንድ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል። ሩቶ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የኢትዮጵያዉ 2018 ዓ.ም. ከገባ ይህ ሁለተኛቸው ነው።
በአፍሪቃ የዲፕሎማሲ ማዕከልነትን የሚቀናቀኑት ናይሮቢ እና አዲስ አበባ በመሪ ደረጃ የሚያደርጓቸው ንግግሮች ቀጣናውን በማረጋጋት ሂደት ምን ሚና ይኖረዋል ትላላችሁ ? ሃሳባችሁን አካፍሉን ።
