ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም የአሜሪካ የኢሚግራንት ቪዛዎች መስጠት ተቋርጧል።
በዚህም የአሜሪካ ዜጋ ልጆች፣ የትዳር አጋሮች እና ወላጆች ጭምር ወደ አሜሪካ ለመሄድ ቪዛ እንደማይሰጣቸው በአሜሪካ የሚኖሩ የህግ ባለሙያቅ አቶ ሙሉአለም ጌታቸው ገልጸዋል።
ይህ ተግባራዊ የተደረገው ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሀገራት ላይ የታወጀውን የጉዞ እገዳ ተከትሎ ነው።
” ይሄ እገዳ ከሁሉም በላይ የአሜሪካ ዜጎችን ከሚስቶቻቸው፣ ልጆቻቸው እና ወላጆቻቸው የሚነጥል ነው ” ሲሉ የህግ ባለሙያው ገልጸዋል።
የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የውጪ ሃገር ዜጎች ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV)ን ጨምሮ ወደ አሜሪካ ሄደው በቋሚነት መኖር ሲፈልጉ የሚሰጣቸው ቪዛ (Immigrant Visa) ሂደት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሃገራት እንደሚቋረጥ አሳውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
