በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደዋል

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 14ኛዉ የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒት የመዝጊያ እና የእውቅና መርሀ ግብር  እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በኢሊሊ ሆቴል እሁድ መጋቢት 7 2017ዓ.ም ተካሄደዋል ።


በመርሀ ግብሩ ላይም ለአገር ውስጥና ለውጪ ተሳታፊዋች እውቅና የተሠጠ ሲሆን  የንግድ ትርዒቱ  የተሳካ እንዲሆን  ድጋፍ ላደረጉ በተጨማሪም  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተሳታፊዋች ሽልማት ተሰጥቷል ።


በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ እንደገለፁት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ የመሪነት ሚና የሚጫወት፣ ጠንካራና ዘላቂ አቅም ያለዉ አቅም እንዲፈጠር  ብሎም ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 14ኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ፤ የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ግብዓቶች በማስተዋወቅ፣ ለአገራችን ኢንዱስትሪ ልማት እድገት፣ ለስራ ፈጠራ እና ለንግድ ስራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት እንዲሁም የሀገር ዉስጥና የዉጭ ኩባንያዎች መካከል የገበያ ትስስር፣የእዉቀትና የልምድ ልዉዉጥ የተደረገበት ከመሆኑ አንጻር  ውጤታማ ነበር፡፡


  ከዚህም ባሻገር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ይህ ኤግዚቢሽን  ከውጭ የመጡ የንግድ አካላት የተሳተፉበት እንደመሆኑ  ልምድ ለመለዋወጥ እና ትስስር ለመፍጠርም ትልቅ ጠቀሜታ ተገኚቶዋል ።

የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ እድሎችን የዳሰሰ የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የንግዱ ማኀበረሰብ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተወከሉ የስራ ኃላፊዋች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...