ከዚህ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህ ቁጥር 1,000 ነበር፤ በተሰራው የስነ ተዋልዶ ጤና ስራ ቁጥሩን መቀነስ ስለተቻለ 141 ደርሷል ተብሏል።
አሁን ያለውን 141 ከአራት ዓመት በኋላ በፈወደ 70 በማውረድ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል።
ይህ የተሰማው በኢትዮጵያ የጽንስና ማህፀን ሐኪሞች ማኅበርና በአፍሪካ የጽንስና ማህፀን ፌዴሬሽን በጋራ ለ34ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ዛሬ በተጀመረው ኮንፈረንስ ላይ ነው።
”በኢትዮጵያ የስነ ተዋልዶ ጤና ውስጥ ካሉ ችግሮች ውስጥ ዘላቂ የስነ ተዋልዶ ጤና ስርዓትን ማሰስ” በሚል በተሰናዳው በዚህ የሁለት ቀን ኮንፈረንስ ከአፍሪካ ሃገራት የመጡ ከ150 በላይ የዘርፉ ሙያተኞችን ጨምሮ ከ1000 በላይ የኢትዮጵያ የፅንስና ማህፀን ሃኪሞች ማህበር አባላት ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ሃይለማርያም ሰኚ ካገቡ ሴቶች መካከል ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ ሴቶች 35 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል።
የእናቶችና የህጻናት ሞት በከፍተኛ መጠን መቀነስ ተችሏል ፣ የእናቶች ጤና መሻሻሎችን አሳይቷል ፣ የፖሊሲ ለውጦች በመደረጋቸው ምክንያት ደህንነቱ ባልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ምክንያት የነበረው የሞት ምጣኔ አሳማኝ በሆነ መልኩ ቀንሷል ያሉት ዶ/ር ሃይለማሪያም፤
ምንም እንኳ እነዚህ እድገቶች እንደተመዘገቡ ቢነገርም ከዚህ ጎን ለጎንም ፈታኛ ሁኔታዎች መኖራቸው አልቀረም ብለዋል።
የስነ ተዋልዶ ጤና መረጃዎች እና አገልግሎቶች አነስተኛ መሆን ፤ በተለይ በገጠሩ አካባቢ ያሉ ወጣቶች ፣ ያላገቡ ሴቶች ፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው እና ሌሎች የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሉ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመድረስ ውሱንነት መኖር ዋንኞቹ ችግሮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት በዘርፉ ሰፊ ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች፣በዚህም የእናቶችና የሕፃናት ሞት በከፍተኛ መጠን መቀነስ መቻሉ እንደ ትልቅ ስኬት ተነስቷል።
ሸገር 102.1
