ከቀናት በፊት በስምንተኛ ዙር በቶሩን ፖላንድ ተካሄዳዉ ፍጻሜዉን ባገኙዉ የዓለም የቤት ዉስጥ የወርቅ ደረጃ ያለዉ የቱር ዉድድር የ1500 ሜትር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ በ2026 የቤት ዉስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቀጥታ ተሳታፊ መሆኗን ያረጋገጠችዉ፣ ብርቄ ሀየሎም በዉጤቱ መደሰቷን ገልጻለች።
አትሌቷ በማህበራዊ የትስስር ገጿ በሰፈረችዉ አጭር መልዕክት፣ “በ 1ሺ 500 ሜትር የቤት ዉስጥ የቱር ዉድድር አጠቃላይ አሸናፊ በመሆኔ ደስ ብሎኛል” ስትል ስሜቷን አጋርታለች።
ብርቄ በፖላንድ ቶሩን የተካሄደዉን የ1500 ሜትር ዉድድር ያካሄደችዉ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኗን ቀደም ብላ አዉቃ መግባቷ አቋሟን የምትለካበትና ከመረሃግብር ሟሟያነት የዘለለ አልነበረም።
በፖላንድ ቶሩን የርቀቱ ዉድድር፣ ከሀገሯ ልጅ ፍሬወይኒ ሀይሎ በመቀጠል በሶስተኝነት ማጠናቀቋም አይዘነጋም። በዚህም በርቀቱ በ27 ነጥቦች ቀዳሚ ሆና አጠቃላይ አሸናፊና የ2026 የዓለም የቤት ዉስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳታፊነቷንም ማረጋገጥ ችላለች።
ባለፈዉ እሁድ በቶሩን ተከናዉኖ በተጠናቀቀዉ የቤት ዉስጥ የቱር ዉድድር ከየ ዲሲፕሊኖቹ አስራ አንድ አትሌቶች አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በኩጃዊ ፖሞርዜ ለሚካሄዶ የዓለም የቤት ዉስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማለፋቸዉን ማረጋገጥ ችለዋል።
ሀገራት በዚህ ሻምፒዮና በአንድ ዉድድር ዓይነት በሁለት አትሌቶች ብቻ የሚወከሉ ቢሆንም እንደ ዚህ ዓይነት ዉድድሮች ለአሸናፊ አትሌቶች የቀጥታ ተሳታፊነት እድልን ሰለሚፈጥሩ ሀገራት ሶስት አትሌቶችን እንዲያሳትፉ እድልን ይፈጥርላቸዋል።
የ2026 የዓለም የቤት ውስጥ ቱር (World Indoor Tour) ተከታታይ ውድድሮች እያንዳንዱ አሸናፊ አትሌት 10,000 የአሜሪካ ዶላር ጉርሻን ያገኛል።
