አሜሪካ የኢራን ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን መታች

Date:

አሜሪካ፤ የዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ በሚተላለፍበት ሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ 16 የባሕር ላይ ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን ጨምሮ በርካታ የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦችን ማውደሟን አስታወቀች።

የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መረጃ፤ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚንቀሳቀሱ 16 ፈንጂ አጥማጆች “ተወግደዋል” ብሏል። ማዕከላዊ ዕዙ፤ መርከቦቹ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ያሳያል የተባለ ቪዲዮም ለቅቋል።

የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን የአሜረካ ጦር ወሽመጡ ተከፍቶ እንዲቆይ ለማድረግ ሌሎች አማራጮችን እያዘጋጀ እንደሆነ ዋይት ሀውስ ገልጿል።

አሜሪካ የአሁኑን ጥቃት የፈጸመችው የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴት በትናንትናው ዕለት እስካሁን ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀናት “እጅግ የከበደው” ቀን እንደሚሆን ከተናገሩ በኋላ ነው።

አንድ ከፍተኛ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ ግን አገራቸው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ረብ የለሽ ዛቻ” እንደማትሸበር ተናግረው ነበር።

መከላከያ ሚኒስቴትሩ ሄግሴት፤ አሜሪካ የኢራንን የሚሳዔል ክምችት፣ የሚሳዔል ማስወንጨፊያ እና የመከላከያ ኢንዱስትሪዎችን የማውደም እቅድ እንደያዘች ተናግረዋል። የኢራን ባሕር ኃይልን ማውደም እና ኢራን በቋሚነት የኒውክሌር መሣሪያ እንዳይኖራት ማድረግም ከግቦቹ መካከል ተጠቅሰዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ኢራን የተኮሰቻቸው መሣሪያዎች ብዛት ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ዝቅተኛው ሆኖ እንደተመዘገበም ገልጸዋል።

የአሜሪካ ጥምር ጦር አዛዦች ሊቀመንበር የሆኑት ጄነራል ዳን ኬይንም በተመሳሳይ፤ የኢራን የባለስቲክ ሚሳዔል ጥቃቶች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል።

ጥቃቶቹ “ከተጀመሩበት ጊዜ አንጻር በ90 በመቶ ቀንሰዋል፤ የአንድ አቅጣጫ ተዋጊ ድሮኖች ደግሞ ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ በ83 በመቶ ቀንሰዋል” ብለዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴት፤ ጦርነቱ ሊያበቃ የሚችልበትን ጊዜ ከመግለጽ ተቆጥበዋል። “አቅማችን ማለቂያ የለሽ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ ጦርነቱ ምን ያህል ይቆያል የሚለው የሚወሰነው ግን በፕሬዝዳንቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...