የግል ትምህርት ተቋም የገቢውን 35% ለመንግስት እንዲያስረክብ የሚያስገድድ ደንብ ወጣ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት በመንግስት ያልተገመገሙ መጻሕፍትን ሲጠቀሙ ወይም ሲሸጡ ከተገኙ፣ ከአጠቃላይ ወርሃዊ ገቢያቸው ላይ 35 በመቶ የሚሆነውን ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ አዲስ ደንብ መዘጋጀቱን ተዘገበ ።

ይህ “ለአንድ ጊዜ ብቻ” ተግባራዊ የሚደረግ የገንዘብ ቅጣት፣ በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በህግ ለማስተካከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን የታለመ መሆኑ ተገልጿል። ረቡዕ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ለባለድርሻ አካላት ውይይት የቀረበው ይህ ደንብ፣ በተለይ ጥብቅ የሆኑ የቁጥጥር ድንጋጌዎችን ይዟል።

ከመጽሐፍ አጠቃቀም ባለፈ፣ የትምህርት ተቋማቱ ከከተማዋ ትምህርት ቢሮ አሰራር ውጪ “የማጠናከሪያ ትምህርት” (Tutorial) ሲሰጡ ከተገኙም ተመሳሳይ የ35 በመቶ የገቢ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ደንቡ “የማጠናከሪያ ትምህርት” የሚለው በክረምት ወይም ከትምህርት ሰዓት ውጪ የሚሰጡ ስልጠናዎችን ሲሆን፣ እነዚህም በተማሪዎችና በወላጆች ፈቃደኝነት ላይ ያልተመሰረቱ ከሆኑ ተቋማቱን ለከፍተኛ ቅጣት ይዳርጋቸዋል። ይህም ትምህርት ቤቶች ካልተገባ የትርፍ ፍለጋ ሩጫ እንዲታቀቡ ለማድረግ ታስቦ የተቀረጸ መመሪያ ነው።

ሌላው ከፍተኛ ቅጣት የሚያስከትለው ጥፋት፣ ትምህርት ቤቶች ከእውቅና ፈቃዳቸው በላይ “የተማሪ ቁጥር” አጭቀው ሲገኙ ነው። አግባብ ካለው አካል ከተሰጠው ደረጃና እርከን ውጪ ተማሪ ይዞ የሚገኝ ማንኛውም የትምህርትና ስልጠና ተቋም፣ የገቢውን 35 በመቶ ቅጣት እንዲከፍል ይገደዳል።

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚገኙ ተቋማት ደግሞ የሰልጣኞችን መረጃ በጥራትና በጊዜው ካላስገቡ፣ ከወርሃዊ ገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግስት እንዲያስረክቡ ደንቡ ያዝዛል።

ይህ አዲሱ ደንብና አብሮት የቀረበው መመሪያ፣ ተቋማቱ የተገኘባቸውን ጥፋት እንዲያስተካክሉ እስከ ሁለት ሳምንት የሚቆይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጥ ይደነግጋል።

በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስተካከያ ያላደረጉ፣ በተደጋጋሚ ጥፋት የሚፈጽሙ ወይም የሚሰጣቸውን ግብረ-መልስ የማይቀበሉ ትምህርት ቤቶች፣ እስከ “ዕውቅና ፈቃድ መሰረዝ” የሚደርስ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተገልጿል። እርምጃውን የመውሰድ ሙሉ ስልጣንም ለአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ተሰጥቷል።

ይህ አዲስ መመሪያ በተለይ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል የሚገመት ሲሆን፣ የትምህርት ተቋማትና የሙያ ብቃት ምዘና ላይ የሚሳተፉ አካላት መብትና ግዴታንም በዝርዝር አካቷል።

ለአንድ ጊዜ ብቻ ተግባራዊ የሚደረገው ይህ የገቢ 35 በመቶ ቅጣት፣ ተቋማቱ ከትምህርት ጥራትና ከአሰራር ደንቦች ጋር ተስማምተው እንዲሰሩ ለማስገደድ የተቀመጠ ጠንካራ የቁጥጥር ስልት መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...