የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ከመጋቢት 24 ጀምሮ የካምቦዲያ፣ የጆርጂያ፣ የግሬናዳ፣ የሌሴቶ፣ የሞሪሸስ፣ የሞንጎሊያ፣ የሞዛምቢክ፣ የኒካራጓ፣ የፓፑዋ ኒው ጊኒ፣ የሲሼልስ እና የቱኒዚያ ፓስፖርት ያላቸው የቪዛ አመልካቾች ይህንን የዋስትና ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
እነዚህ አሀገራት አስቀድሞም 38 በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ወደተካተቱበት ዝርዝር መጨመራቸው ነው የተገለጸው፡፡
ክፍያው የቪዛ ማመልከቻው ውድቅ ከተደረገ ወይም ቪዛው ተሰጥቶት ግለሰቡ የቪዛውን ሕግጋት አክብሮ ከተገኘ ተመላሽ ይደረጋል ሲሉ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
