የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Date:

39 አባል ሀገራት እና ሌሎች ባለድርሻዎች የሚሳተፉበት የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም (ARC-COP 16) ጉባዔ ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጉባኤው በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጿል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ራሷን ለመቻል የምታደርገው ጥረትና የመጣው ውጤት በመድረኩ በተሞክሮነት ይቀርባል።

የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን ለመፍታት ከሚሰራባቸው መስኮች መካከል በሰብዓዊ ድጋፍ ራስን መቻል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው÷ በመድረኩ መግባባት ለመፍጠር ምክክር ይደረጋልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያከናወች ስራ እና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማሟላት የተገበረቻቸው ተግባራት ለጉባዔው አስተናጋጅነት ተመራጭ እንዳደረጋት አንስተዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ በማድረግ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...