የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኩዩሪቲ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

Date:

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኩዩሪቲ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፅድቋል።

በም/ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ፈቲህ መሀዲ (ዶ/ር) ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል።

በማሻሻያ አዋጁ መሠረት የሚዘረጉ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች አሁን ያሉትን የደህንነት ስጋቶች የሚፈታ ስለመሆኑ በውሳኔ ሀሳቡ ተገልጿል።

አዲሱ አዋጅ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን መለኪያ መሠረት የተሻለ የአቪዬሽን ሴኩዩሪቲ መገንባት የሚያስችል ነው ተብሏል።
እንደ ሀገር ከዚህ በፊት የነበረውን መልካም ገጽታ ለማስቀጠል የሚያስችል ማሻሻያ አዋጅ ስለመሆኑም ዶ/ር ፈቲህ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እንደ ሀገር ሲያስመዘግብ የነበረውን ከፍተኛ ውጤት ለማስቀጠል ወቅቱን የዋጀ የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ነው የተባለው።

በዚህም ለዓለም ማህበረሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አስተማማኝና ቀልጣፋ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተብራርቷል።

ነባሩ አዋጅ 432/1997 ከ20 ዓመታት በላይ ያለማሻሻያ የቆየ በመሆኑ አዲሱ አዋጅ ዘመኑ ያመጣቸውን ውስብስብ ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስለመሆኑም ተገልጿል።

የምክር ቤቱ አባላትም የአዋጁን አስፈላጊት በሚመለከት አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀጣይ ገቢ አሰባሰብን ጨምሮ አፈፃፀም ላይ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ያሏቸውን ሀሳቦች አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ የቀረበውን ረቂቅ፣ አዋጅ ቁጥር 1412/2018 አድርጎ በ2 ተቃውሞና በ2 ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ማፅደቁን ተገልጿል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...