የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 54 ‹‹አስገዳጅ›› ህጎችን አፀደቀ

Date:


የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃዎች ቦርድ ባካሄደው 5ኛው መደበኛ ስብሰባው፤ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች ደኅንነት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው የተባሉ 66 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን መርምሮ አጽድቋል።

የደረጃዎች ዝግጅት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ይልማ መንግስቱ፤ እነዚህ ደረጃዎች በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በምግብና ግብርና እንዲሁም በኮንስትራክሽንና ሲቪል መሐንዲስነት ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው ብለዋል።

ከጸደቁት 66 ደረጃዎች መካከል 24ቱ አዳዲስ ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ 42ቱ ደግሞ ከጊዜው የቴክኖሎጂ ዕድገትና ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ ተደርገው የተሻሻሉ ናቸው።

ቦርዱ ካጸደቃቸው ደረጃዎች ውስጥ 54ቱ ‹‹አስገዳጅ›› ሆነው የወጡ ሲሆን፤ ይህም አምራቾችና አስመጪዎች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ከመልቀቃቸው በፊት የግድ እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት እንዳለባቸው የሚያመለክት ነው።

ኢንስቲትዩቱ እነዚህ ደረጃዎች የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ በዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...