በአዝናኝነቱ እና ልብ አንጠልጣይነቱ ለ38 ሳምንታት ሲጓዝ የሰነበተው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተቋጨ። አርሰናልን በአሸናፊነት፣ ዎልቭስን፣በርንለይን እንዲሁም ዌስትሃምን ወደ ታችኛው የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ አውርዶ መቋጫው አግኝቷል።
የውድድሩን አመት 27 ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ኖርዌያዊው አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ ሱጎናፀፍ። ፖርቹጋላዊው የዩናይትድ ምተሐተኛ ብሩኖ ፈርናንዴዝ 21 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ በማቀበል የምን ጊዜውም ታላቅ የመሀል ሜዳ ተጫዋች መሆን የቻለበትን ምሽት አሳልፏል።
ኖርዝ ለንደን በአርሰናል ደጋፊዎች ፌሽታ ብቻ አልደመቀችም በተቀናቃኛቸው ስፐርስ ደጋፊዎች አሸብርቃለች። ኤቨርተንን በማሸነፍ በሊጉ መትረፋቸውን ያረጋገጡት ቶተንሃሞች በቀጣዩ የውድድር አመት በብዙ መለወጥ ይኖርባቸዋል።
የምዕራብ ለንደኖቹ ዌስትሃሞች ምንም እንኳን ሊድስን 3-0 በሆነ ውጤት ቢረቱም የ15 አመት የሊግ ቆይታቸው በዚህ አብቅቷል።
ሊጉን በያዝነው ውድድር አመት የተቀላቀሉት ሰንደር ላንዶች ቼልሲን በደጋፊያቸው ፊት 2-1 በሆነ ውጤት በመርታት የቀጣዩ ዘመን የአውሮፓ ሊግ ተካፋይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
