“ ህመም ይሰማኛል ”
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጨዋታው የነበረውን ዳኝነት ተችተዋል።
ማዱኬ ላይ የተሰራው ጥፋት “ ለእኛ ፍፁም ቅጣት ምት ነበር “ ያሉት ሚኬል አርቴታ ዳኛው መሳሳቱን ገልጸዋል።
“ ዳኛው ለእነሱ ፍፁም ቅጣት ምት ለመስጠት ወስኖ ለእኛ ግን የተለየ ውሳኔ ሰጥቷል “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ወቅሰዋል።
ምን እየተሰማቸው እንደሆነ ሲጠየቁም “ ህመም እየተሰማኝ ነው “ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
“ ፒኤስጂ እና ሉዊስ ኤንሪኬን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ የአለም ምርጥ ቡድን ናቸው ” አርቴታ
@tikvahethsport
