የዓለም ሜትሮሎጂ የአዲስ ኤሊኒኖ ክስተት

Date:

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት (WMO) ባወጣው መግለጫ፣ አዲስ የኤሊኖ (El Niño) ክስተት እንደሚፈጠር ያረጋገጠ ሲሆን ይህ ክስተት ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2026 ባሉት ወራት ውስጥ የማጋጠም ዕድሉ 80 በመቶ መሆኑን ገልጿል።

የፓስፊክ ውቅያኖስ የውስጠኛው ክፍል ውሃ ከተለመደው በላይ ሙቀቱ መጨመሩ ለዚህ አዲስ የኤሊኖ መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

ይህ አዲስ የኤሊኒኖ ክስተት በኢትዮጵያ ዋነኛ የምግብ ምርት ወቅት በሆነው የሰኔ-መስከረም የክረምት ዝናብ ላይ ከመደበኛ በታች (ዝቅተኛ) ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል የሚል ትንበያ ተቀምጧል።

ይህም በሀገራችን ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የክረምት ዝናብ ላይ ከመደበኛ በታች (ዝቅተኛ) ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል።

ከዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከመደበኛው በላይ የሆነ ከፍተኛ ሙቀት የሚያስከትል መሆኑንና ይህም የአፈር እርጥበትን በማድረቅ በሰብልና በከብቶች ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ተሰግቷል።

ኤሊኒኞ እየበረታ ሲሄድ ከዓመቱ ማጠናቀቂያ (ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ) ባሉት ወራት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ቆላማ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ እና የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል።

ሀገራት ይህንን አዲስ የኤሊኖ መከሰት እንደ አስቸኳይ የአየር ንብረት ማስጠንቀቂያ ወስደው የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ሥራዎችን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...