የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

Date:

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት አገልግሎት ላይ የቆየውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-ሥርዓት ለመተካት፣ አዲሱን የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 በመጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማፅደቁ ይታወሳል።

​ይሁን እንጂ አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ወጥቶ ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት፣ የመጨረሻዎቹ የቃላት ማስተካከል እና የህግ እርማት ስራዎች በምክር ቤቱ እና በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል በጥንቃቄና ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

​ህጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ለህዝብ ይፋ ባልተደረገበት ሁኔታ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሲዘጋጁ የነበሩ ረቂቅ ሰነዶችን ለተለያዩ ሙያዊ፣ ተቋማዊ አገልግሎቶች እንዲሁም ለስልጠናዎች በመጠቀም ረገድ የተሳሳቱ አዝማሚያዎች መታየታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...