ሚድሮክና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ80 ሚሊየን ዶላር ብድር ተፈራረሙ

Date:


ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የ80 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የረጅም ጊዜ የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አህመድና የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዚዳንት ኢትዮጲስ ተፈራ በኬንያ ናይሮቢ ነው የተፈራረሙት።

አቶ ጀማል አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም ጋር የተጀመረው አጋርነት የሀገሪቱን የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ለማዘመን እንዲሁም በኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ኢትዮጲስ ተፈራ በበኩላቸው÷ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የአገልግሎት ዘርፉን የበለጠ እንዲያዘምንና ተጨማሪ የሥራ እድል እንደፈጥር ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

በተገኘው ገንዘብ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴልን በዘመናዊ መልኩ እንደሚያድስ ተገልጿል።

በሸራተን ደረጃ አዲስ ሆቴል እንደሚገነባም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።

:: :: :: :: :: :: ::
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...