ቆሻሻን ወደ ሚሊዮን ብር ካፒታል የቀየሩ የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ተመረቁ

Date:

በኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት፣ በአየር ንብረት ፈጠራ እና ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በ ማዋል ዙሪያ አዳዲስ የቢዝነስ መፍትሄዎችን ያመነጩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2018 አ. ም ተመርቀዋል::

“ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ” (Reach for Change Ethiopia) የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ከ”አይ.ኬ.ኢ.ኤ ፋውንዴሽን” (IKEA Foundation) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ፣ በ”ሕንጻ ግንባታ ቆሻሻ እና ሰርኩላር ኢንተርፕራይዞች ፕሮግራም ስር የሰለጠኑ የ2025 ሰልጣኞች ተመርቀዋል በተመሳሳይም ወቅትም የ2026 የቢዝነስ ማሳደጊያ (Incubator) ፕሮግራምን የሚቀላቀሉ አዳዲስ ወጣቶች አቀባበል ተደርጐላቸዋል::

በዕለቱ የተመረቁትና ድጋፍ የተደረገላቸው ስራ ፈጣሪዎች በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች የተከፈሉ ሲሆን

33 በሃሳብደረጃላይየነበሩድርጅቶች የፈጠራ ስራቸውን ወደ ተግባር በመቀየር የራሳቸውን ቢዝነስ ይፋ እንዲያደርጉ የቴክኒክ ስልጠና እና እያንዳንዳቸው የ 200 ሺህብር የገንዘብ ድጋፍ አግኝተዋል።

በሌላ በኩል 8 ቀደም ሲል ስራ ላይ የነበሩና እራሳቸውን በሃሳብም ሆነ በፋይናንስ ለማሳደግ በሂደት ላይ ያሉ ድርጅቶች እስከ 1.5 ሚሊዮንብር የሚደርስ ከፍተኛ ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል።

ይህ ፕሮግራም በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው ወጣቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን በገበያ ላይ ውጤታማ ማድረግ እንዲችሉ “ቢዝነስ እንዴት እንደሚመራ” (Business Run) እና የገንዘብ አጠቃቀም ላይ አቅማቸውን በመገንባት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በፕሮጀክቱ ውስጥ ከተካተቱት ወጣቶች መካከል 60 በመቶየሚሆኑት የነበራቸውን የፈጠራ ህልም በተግባር ማሳካት ችለዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ያዘጋጇቸው ተግባራዊ የአካባቢ ጥበቃ እና የቆሻሻ አያያዝ የፈጠራ ስራዎች ለጉብኝት የቀረቡ ሲሆን በዘርፉ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ዙሪያ የሚያጠነጥን የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ላይ እንደተነሳው በአሁኑ ወቅት በህብረተሰቡ ዘንድ ቆሻሻንበድጋሚጥቅምላይማዋል” (Recycling/Circular Economy) ላይያለውግንዛቤገናአነስተኛመሆኑ በዘርፉ ለተሰማሩ ስራ ፈጣሪዎች ዋነኛ ማነቆ መሆኑ ተጠቅሷል።

ይህንን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላትና የገበያ ትስስሩን ለማጠናከር የመንግስትና የግል ዘርፉ ትብብር ወሳኝ መሆኑ በአፅንኦት ተሰቶታል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...