አሐዱ ባንክ “አሐዱ ለኩሉ” እና ”ማኅደር” የተባሉ ሁለት መተግበሪያዎችን በይፋ አስጀመረ

Date:

ሁለቱ  የሞባይል መተግበሪያዎች  የባንኩን የዲጂታል ባንኪንግ  አገልግሎት ጉዞን ይበልጥ እንደያጠናክሩለት እንደሆኑ ተነግሯል።

“አሐዱ ለከሉ “የተባለው  የሞባይል ባንኪንግ  መተግበሪያ  ደንበኞች ሞባይል  ስልካቸውን በመጠቀም የሒሳብ መረጃቸውን እንዲያዩ፣ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ፣ እንዲያስተዳድሩ፣ የገንዘብ ፍሰታቸውን እንዲከታተሉ እና የተለያዩ የክፍያ አገልግሎቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን በባንኩ መግለጫ ተጠቅሷል።

የደንበኞችን የአጠቃቀም ሒደቶች በመተንተን በብዛት የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶች በቅድሚያ እንዲያዩ የሚያስችል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ሥርዓትን በውስጡ ያካተተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፤ ደንበኞች ሳምንታዊ የወጪ ሪፖርታቸውን/ መግለጫዎችን በማየት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን እንዲገመግሙ እና የተሻለ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲወስኑም ያግዛቸዋል ተብሏል።

“አሐዱ ለኩሉ” በዓለም አቀፍ የደኅንነት መሥፈርቶች መሠረት የተገነባ ሲሆን፤ ማጭበርበርን እና የሳይበር ስጋቶችን ለመከላከል የተለያዩ የደኅንነት ሥርዓቶችን ያካተተ መተግበሪያ ነው።

”አሐዱ ለኩሉ” በአሐዱ፡ባንክ የውስጥ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ እና በቀጣይም እየተሻሻለ የሚሔድ መተግበሪያ ሲሆን፤ ይህም ባንኩ ቴክኖሎጂን የመፍጠር አቅሙ በአያሌው እንዳሳደገ ያሳየ መተግበሪያ ነው፡፡

“ማኅደር”  በሚል መጠሪያ በዛሬው እለት አሐዱ ባንክ በይፋ ያስጀመረው መተግሪያ  ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ክዋኔዎችን የሚመዘግቡበት እና የሚተዳደሩበትን፣ ብድር የሚጠይቁበትን፤ የንግድ መድን ሽፋን የሚያገኙበትን አጠቃላይ ሥራዎች በአንድ ያቀፈ  ነው ተብሏል።

“ማኅደር የንግድ ተቋማት ራሳቸውን በዲጂታል መንገድ  እንዲመዘግቡ ፤ የሽያጭ፣ የወጪ እና ሌሎች ከንግድ ሥራቸው ጋር የተያያዙ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን የሚመዘግቡበት የዲጂታል የገንዘብ መመዝገቢያን (Cash Book) አብሮ ያካተተ መሆኑ ተጠቅሷል።

“ማኅደር” የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት የንግድ አቅማቸውንና የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መሠረት በማድረግ ብቻ ካለምንም የብድር ማስያዣ  እስከ 600,000 ብር ድረስ የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያችላል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...