‹‹ብዕርና ባሩድ›› የተሰኘው የታዋቂው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ አዲስ መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስንክሳር በጥልቀት የሚዳስስ፣ በኢትዮጵያ የ 70 ዓመት ፖለቲካ ውስጥ በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ ጉልህ ሚና የተጫወቱ፣ የአሥራ ስምንት ታዋቂ ፖለቲከኞችን ሃሳብ ‹‹ከፈረሱ አፍ›› በሚል ክፍል ስር በጥሩ ኹኔታ አቅርቧል፡፡
ከዚህ ቀደም፣ ‹‹ሁሉም በየፊናው የመሰለውን ምልከታውን ያቀርባል እንጂ፣ እንደ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ የበርካታ የፖለቲካ ልሂቃንን ክርክር በአንድ ጥራዝ ስር አቅርቦ ያከራከረ ድርሳን የለም›› ተብሎለታል፡፡
የአንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ፤ ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት፣ በአምስት ምዕራፎች በ 500 ገጽ ተሠናድቶ በ 850 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
‹‹ብዕርና ባሩድ›› የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅጡ ለመረዳት ለሚታትሩ፣ ለተመራማሪዎችና ለሀገራቸው የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ለሚሹ ሁሉ፣ በጥንቃቄና በሚዛናዊነት የቀረበ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ፣ በቅርቡ በጀርመን አገር ፍራንክፈርት ከተማ እና በአሜሪካን አገር ታትሞ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እና በካናዳ ቶሮንቶ ለንባብ ቀርቧል፡፡
በአማዞንም በሕትመት- በኪንድል (Paparback) እና በኢ-ቡክ (e-book) ታትሞ ለአንባቢዎች እነኾ ቀርቧል፡- https://a.co/d/03bbV8Zy
አሁን ደግሞ ለሀገር ውስጥ አንባቢዎች እነኾ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
