በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ፣ የአንድ መምህርና ገና ዛሬ ከኮሌጅ የተመረቀች ባለቤታቸው ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ተሰማ። ሕ
ይወታቸው ያለፈው መምህር አብሪሃም ግዛው እና ባለቤቱ መምህርት ራሄል አክሊ መሆናቸው ታውቋል።
አደጋው የደረሰው ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ገደማ፣ ከቦንጋ ወደ ሺሺንዳ በመጓዝ ላይ በነበረና የሰሌዳ ቁጥሩ 00582 በሆነ የ”ዶልፊን” የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው።
መኪናው ዋና ቦላ በተባለ ቀበሌ ላይ መንገድ ስቶ 50 ሜትር ገደል ውስጥ በመግባቱ ጥንዶቹ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።
መምህርት ራሄል የኮሌጅ ምረቃዋን አጠናቃ በደስታ ወደ ቤት እየተመለሰች ነበር።
በአደጋው ሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ በዲንቢራ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
