በኢራቅ መዲና ባግዳድ በተካሄደ መጠነ-ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ፣ በሀገሪቱ የፓርላማ አባል ሂንድ አል-አባሲ መኖሪያ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 57 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ እና 27 ኪሎ ግራም ንጹህ ወርቅ መያዙ የሀገሪቱ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ይበልጥ መነጋገሪያ የሆነው ግኝት ግን በወርቅ የተለበጡ የውስጥ ሱሪዎች በክፍላቸው ውስጥ መገኘታቸው ነው።
ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ከመንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
የጠቅላይ ሚኒስትር አሊ አል-ዛይድ መንግስት የመንግስት ፈንድ ምዝበራን ለመግታት በጀመረው በዚህ የነጋሪት ፍተሻ እስካሁን የፓርላማ አባላትን እና ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በኢራቅ ጠቅላይ የፍርድ ቤት ምክር ቤት ይፋ የተደረገው ይሄው ዘመቻ፣ የቀድሞው ምክትል የነዳጅ ሚኒስትርንም ያካተተ ሲሆን፣ ከተጠርጣሪዎቹ እጅ 10 ሚሊዮን ዶላር፣ 3 ቢሊዮን የኢራቅ ዲናር፣ የጦር መሳሪያዎች እና 40 የሚደርሱ ህንጻዎች ተወርሰዋል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማይኖርና ምርመራው ሰፊ መዋቅሮችን እያካተተ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
