ሩሲያ በፈጸመችው ሰፊ የአጸፋ ጥቃት በርካታ ወታደራዊ ፋብሪካዎች ተመቱ

Date:

የሩሲያ ጦር ኃይል በኪዬቭ እና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ እና የኃይል ተቋማት ላይ ሌሊቱን ሙሉ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሙን የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የረጅም ርቀት ትክክለኛ መሣሪያዎችን እና አጥቂ ድሮኖችን በመጠቀም የተፈጸመው ይህ ጥቃት፤ በሩሲያ ግዛት ላይ ለተሰነዘሩት የዩክሬን የሽብር ጥቃቶች የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ ነው ተብሏል።

በኪዬቭ ውስጥ የተመቱ ዒላማዎች

▪️ ኪዬቭ-71 የኢንዱስትሪ ፋብሪካ (አብሪስ ፒቲ)፦ የረጅም ርቀት የስለላ ድሮኖችን፣ እንዲሁም የቴሌሜትሪ እና የኦፕቲካል መሣሪያዎችን ያመርታል።

▪️ ኪዬቭ-1 መገጣጠሚያ ፋብሪካ፦ ለዩክሬን ጦር ኃይል የረጅም ርቀት ድሮኖችን እና የራዳር መሣሪያዎችን ያመርታል።

▪️ ኪዬቭ-79 የኢንዱስትሪ ፋብሪካ፦ የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን፣ የመከላከያ አካላትን፣ እንዲሁም ለሚሳኤል እና ድሮኖች የሚሆኑ ተተኳሽ ራሶችን ያመርታል።

▪️ ኪዬቭ መርከብ መገንቢያ ‘ጂዩርዛ-ኤም’ የተሰኙ የመድፍ ጀልባዎችን የሚገነባ እና ሰው አልባ አጥቂ የውሃ ላይ መንኮራኩሮችን መጠገኛ።

▪️የክቫንት መሣሪያዎች ፋብሪካ፦ የተኩስ መቆጣጠሪያ ሥርዓቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ መከላከያ ዘዴዎችን፣ የናቪጌሽን መሣሪያዎችን እና የ’ኔፕቱን-ኤምዲ’ ሚሳኤል አካላትን ያመርታል።

በኪዬቭ ክልል የተመቱ ዒላማዎች፦

▪️ የዙሊያኒ ሚሳኤል መገጣጠሚያ ፋብሪካ (ቪዛር)፦ የፀረ-አውሮፕላን ሥርዓቶችን፣ የአቪዬሽን አካላትን እና የረጅም ርቀት ድሮኖችን ያመርታል፣ ይጠግናልም። በጥቃቱ ሳቢያ ተከታታይ ፍንዳታዎች ተስተውለዋል።

▪️ የቪሽኔቮዬ የነዳጅ ዴፖ፦ ለግንባር መስመሮች አስቸኳይ አቅርቦት የሚውል ቤንዚን እና ዲዚል የሚቀመጥበት ቁልፍ የማከማቻ ተቋም።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...