ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ እየተካሄደ ባለው የኔቶ (NATO) ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አሜሪካ በኢራን ላይ የሰነዘረችውን የቅርብ ጊዜ ወታደራዊ ጥቃት በጽኑ ተከላክለዋል።
ትራምፕ ኢራን እሱን ለመግደል ባዘጋጀችው “የግድያ ዝርዝር” (kill list) ላይ “ቁጥር አንድ” ኢላማ ማድረጓን በይፋ የገለጹ ሲሆን፣ ሁኔታውን ሲያስረዱም፦ “እኔም ብሆን ነገ ልጠፋ እችላለሁ” በማለት ከፍተኛ ስጋት እንዳለ ጠቁመዋል።
አክለውም የኢራንን መሪዎች “ቆሻሻዎች” (scum) ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን፣ የቀድሞዎቹ የኢራን መሪዎች የገጠማቸው ዕጣ ፈንታ አሁኖቹንም ሊገጥማቸው እንደሚችል በማስጠንቀቅ “እነሱም ቢሆኑ ነገ ሊጠፉ ይችላሉ፤ ማን ያውቃል!” ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለተሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት መከላከያ ሲያቀርቡ፦ “ለሀገሬና ለዓለም ትክክለኛውን ነገር ነው ያደረግኩት” ማለታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።
ምንም እንኳን ትራምፕ ስለተባለው “የግድያ ዝርዝር” ያቀረቡት ተጨባጭ ማስረጃ ባይኖርም፣ ንግግራቸው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ ወደ ከፋ ደረጃ አሸጋግሮታል።
