የትግራይ ክልል ግጭት አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

Date:

በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ  እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ  አሳስበዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል።

የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ የሰብአዊ መብት መርማሪ ቡድኖች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤክስፐርቶች ኮሚሽን እና የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝብ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ሌሎች የሥራ ዘመናቸው ከተቋረጠ በኋላ ክትትሉ መዳከሙን አምነስቲ ጠቅሷል።

በተጨማሪም ባለፉት ሁለት ወራት በትግራይ ክልል ባለስልጣናት በኩል ነፃ መገናኛ ብዙሃንን ማፈን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለግዳጅ ውትድርና መመልመል እና የእንቅስቃሴ ገደቦች ማድረግን የመሳሰሉ አሰራሮች መስፋፋታቸውን የሰብአዊ መብት ተቋማት መዝገባቸውን አውስቷል።

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ...