የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ ነዉ

Date:

በኢትዮጵያ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር እና ተኪ ምርቶች ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እየታየ ያለው ዕድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና የሀገር ውስጥ ምርት አቅምን ለማጠናከር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚንስቴር የምግብ እና መጠጥ ምርምር እና ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ደበበ ወርቁ ገልፀዋል።

ስራ አስኪያጁ የሀገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ አዎንታዊ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል ያሉ ሲሆን፥በተለይም እንደ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ የጣፋጭ ምርቶች እና እሴት የተጨመረባቸው አግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶች ጥራታቸውና የገበያ ድርሻቸው እየጨመረ ይገኛል ብለዋል ።

የተኪ ምርቶችን ማብዛትና የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት፣ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን፣ አቅርቦትን ለማረጋገጥና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና እንዳለውም አመላክተዋል።

በተጨማሪም በዘርፉ የሚታዩትን የግብዓት እጥረቶችና የውጭ ገበያ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም መንግስትና ባለድርሻ አካላት ምርታማነትን በማሳደግና ለምርቶች ተጨማሪ እሴት በመፍጠር ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ይፋ አደረገ

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከአሁን በፊት ከሦስተኛ...

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...