የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ264 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን ገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ስምንት ወራት ከ264 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለደንበኞች ማቅረቡን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።

717 ሺህ ደንበኞች በዲጂታል አማራጭ የብድር ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተቋሙን የስምንት ወራት አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባንኩ ብድርን ከማስፋፋት እና የዜጎችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር አዳዲስ የብድር አይነቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

በዚህም ባንኩ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 264 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞቹ ማቅረቡን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 88 ነጥብ 2 በመቶው የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

እደ ኢዜአ ዘገባ ጠቅላላ የተሰጠ የብድር መጠን ብር 1 ነጥብ 39 ትሪሊዮን በር መድረሱንም ጠቁመዋል።

የብድር ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር ባንኩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በዲጂታል አማራጭ ብድሮችን እያቀረበ መሆኑን ነው ያስረዱት።

ፕሬዝዳንቱ በዲጂታል አማራጭ ባለፉት ስምንት ወራት አጠቃላይ ብር 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብድር ማቅረብ መቻሉንና በፈረንጆች እስከ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2025 ድረስ 717 ሺህ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...