ዋልያዎቹ ከሞዛምቢክ ጋር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከቀኑ 10፡00 በባህር ዳር ስታዲየም ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋል።

በምድቡ ውስጥ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉትን ሁለት ቡድኖች ለመለየት ወሳኝ በሆነው በዚህ ጨዋታ፣ ሁለቱም አሰልጣኞች ሦስቱንም ነጥቦች ለማግኘት እንደሚጫወቱ ከጨዋታው በፊት በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ቡድን ድል ከተቀዳጀ፣ ወደ 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ያለውን ዕድል ማስፋት ይችላል።

የዛሬው ከሞዛምቢክ ጋር የሚደረገው ጨዋታና በቀጣይ ከሱዳን ጋር በሜዳው የሚደረጉት ጨዋታዎች ለዋልያዎቹ እንደ ፍጻሜ የሚቆጠሩ ወሳኝ ፍልሚያዎች ናቸው።

ኢትዮጵያና ሞዛምቢክ በኢትዮጵያ ምድር ሲገናኙ የዛሬው ጨዋታ የመጀመሪያቸው ሲሆን፣ በአጠቃላይ ሁለተኛ የእርስ በርስ ግንኙነታቸው እንደሚሆን ተገልጿል።

ዋልያዎቹ ዛሬ ድል ከተቀዳጁ በምድቡ ያላቸውን ደረጃ ወደ ሁለተኛ ከፍ ማድረግና ነጥባቸውን ወደ ስድስት ማድረስ ይችላሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...