በውቅሮ ከተማ ወጣት ሊድያን የገደለዉ ግለሰብ ተፈረደበት

Date:



ከወራት በፊት በውቅሮ ከተማ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል የበርካቶችን ልብ የሰበረ ነበር። ወጣት ሊዲያ አግብታ ለወግ ማረግ በቅታ ልጆችን አፈራበታለው ያለችው ትዳር ባልተጠበቀ ሁኔታ ህይወቷን አሳጥቷታል። ሰርጓ በተደግሰ በአራት ቀናት ልዩነት የህይወቴ አጋር የልጆቼ አባት ባለችው ሰው ግድያ እንደተፈፀመባት ተረጋግጧል።

የወጣት ሊድያ አለም ግድያ ተከትሎ  ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2017 በውቅሮ ከተማ የሚገኘውን የምስራቃዊ ዞን መካከለኛ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት በወጣት ሊድያና ባለቤቷ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሟችን ሁለት አይኖች ከመሞቷ በፊት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በማውጣት ጎሮሮዋን አንቆ እንደገደላት መረጋገጡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 539(1) ሀ መሰረት ተከሳሽ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ብይን ሰጥቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...