የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ መገኛ የቸገራቸዉ የልማት ተነሺዎች

Date:

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የልማት ተነሺ ፋይሎችን በማዘግየቱ እንዳሳሰባቸው የገለፁ ነዋሪዎች የፋይሎቹ ባለቤቶችና ህጋዊ ወኪሎች ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ለድሬዳዋ ከንቲባ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ቢሞክሩም ፈጽሞ እንደማይቻል እና የከንቲባው የአገልግሎት ቀን በግልጽ እንደማይታወቅም ጭምር ለመሠረት ሚድያ አስረድተዋል።

“የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሲያስተናግዳቸው የነበረውን የልማት ተነሺ ፋይሎች ለሁለት ዓመታት በማገድ የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ቤተሰቦች እና ዘመዶች ግን እየተስተናገዱ ነው” በማለት ተናግረዋል።

“ህጋዊ ወኪል እና የፋይሉ ባለቤቶች ሲጠይቁ ግን ታግዷል ይባላሉ፣ ከንቲባው ነው ያገደው ምንም ማድረግ አንችልም እያሉ መልስ ይሰጣሉ” ብለው ለሚድያችን ቃላቸውን የሰጡ እነዚህ በርከት ያሉ ነዋሪዎች አብዛኛው የልማት ተነሺ፣ ህጋዊ የፋይሉ ባለቤቶችና ወኪሎች አቤቱታ የሚያቀርቡበት ቦታ አጥተው እየተንከራተቱ እንዳሉ ተናግረዋል።

“ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አቤቱታ ለማቅረብ ብንሞክርም በተደጋጋሚ ፈጽሞ ማግኘት እንደማይቻልና በግልጽ የተቀመጠ የአገልግሎት ቀን ከንቲባው እንደሌለው ተነግሮናል” ብለው ለመሠረት ሚድያ የተናገሩት ነዋሪዎች ከንቲባው ባጋጣሚ ቢሮ ቢገኙ እና ለማናገር ቢሞክሩ እንኳን የድሬዳዋ ከተማ አድማ በታኝ ፖሊሶች ተገልጋዮችን እየደበደቡ እንደሚመልሱ ጠቁመዋል።

“ከንቲባውን ሊያገኙ የሚችሉት ሰዎች ጥቂት ባለሀብቶች እና የገጽታ ግንባታ ላይ ያሉ የሶሻል ሚዲያና የሚዲያ ሰዎች ብቻ ናቸው” ብለዋል። 

በርካታ መፈታት ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ የሚጠቅሱት ነዋሪዎቹ የልማት ተነሺዎች የምትክ መሬት ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚፈልግ እንዲሁም በአጠቃላይ የድሬዳዋ ህብረተሰብ የተለያዩ ቅሬታውን ማቅረብ ስላልቻለ የከንቲባው የአገልግሎት ቀን በግልጽ ማወቅ እንፈልጋለን በማለት ተናግረዋል።

በዚህ ዙርያ ከንቲባ ከድርን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፣ ምላሽ ከሰጡን ይዘን እንመለሳለን።

@MeseretMedia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...