የፋሲካ በዓል ሰላማዊ እና የተረጋጋ ነበር

Date:

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዩ ኤፍ ኤም እንዳሳወቀው መደበኛ ከሚባሉ ቀላል ስርቆቶች በስተቀር ከዓሉ ጋር በተገናኛ ምንም ከባድ ወንጀል አልተፈጸመም ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፤ ጠጥቶ ማሽከርከር የበዓላት ወቅት ዋነኛ የአደጋ መንስዔ ነው በመሆኑም ፖሊስ ኮሚሽኑ ባደረገው ጠንካራ ቁጥጥር 1 ሺህ 72 ፍተሻዎች በማድረግ 33 አሽርካሪዎች ከመጠን በላይ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ ተይዘው በደንብ መተላለፍ ቅጣት ተላልፉባቸዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ኮማንደር ማርቆስ የተለያዩ የደንብ መተላለፍ የፈጸሞ ሌሉች 99 አሽርካሪዎች ላይም እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡41 አሸከርካሪዎችን ደግሞ በምክር አልፈናቸዋል ነው ያሉት ፡፡

በአዲስ አበባ በባዕሉ ዋዜማ በቦሌ ወረዳ 14 ገርጂ አከባቢ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበሩ ዕድሜያቸው 50 የሚሆን ሰው ተገጭተው ህይወታቸው ማለፉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...