ዝምተኛው ገዳይ ካርበን ሞኖክሳይድ(CO) (የከሰል ጭስ)

Date:

✍ አብዛኞቻችን  በቤታችን ውስጥ ከሰል የማጨስ ልምድ አለን፡፡ ታዲያ ይህ በቤታችንን የምንጠቀምበት ጭስ በአግባቡና በጥንቃቄ ካልያዝነው ለዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአንጎል ውድመትና የልብ በሽታን ሲያጋልጥ ባስ ሲልም ሕይወታችንን ሊያሳጣን የሚችል አደገኛ ጋዥ ነው::

✍ እንደ አሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል መረጃ መሠረት የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ በአይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ ነው፡፡

👉ካርበን ሞኖክሳይድ የሚፈጠረው ጋዝ፣ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው የሚፈጠር ነው፡፡

✍የእንጨት ከሰል (charcoal) የመኪና ጭስና ሲጋራ ይህንኑ ካርበን ሞኖክሳይድ በማመንጨት ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰልን ጨምሮ የካርበን ምንጭ የሆኑ እንደ ጋዝ ስቶቭ፣ውሃ ማሞቂያ፣ የቤት ማሞቂያ፣የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች በሙሉ በአግባቡ ካልተገጠሙ፣በአግባቡ ካልተጠገኑና ነፋስ የማያገኛቸው ጥብቅብቅ ያለቦታ ከተቀመጡ ችግሩን ሊያከትሉ ይችላሉ፡፡

✍የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ ወደ ውስጣችን በምንስበብት ወቅት በቀጥተ በደማችን ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ሕዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለለተያዩ የሰውነታችን ክፍል ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ካርበኦክሲሄሞግሎቢን ይሆናል፡፡

👉ይህ ከሆነ በኃላ ደማችን ኦክሰጅን መሸከሙን ያቆማል፡፡ በዚህ የተነሳ ሕዋሳቶቻችንና የሕዋሳቶቸችን አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ይሞታሉ፡፡ህይወታችንንም እናጣለን::

✅በመሆኑም  በከሰል ጢስ  ምክንያት በርካቶች   በዝምታ እየሞቱ  በመሆኑ ጥንቃቄ እናድርግ የሚለው ምክራችን ነው::

@entrance_tricks

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...