የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በአለም ላይ እየጨመረ በመጣዉ በስደተኞች ቁጥር በኩል ወቅታዊ መረጃን በዛሬዉ እለት በሰጠበት ወቅት ነዉ ይህንን ያለዉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ለፀጥታው ምክር ቤት ሁኔታዉን ሲገልጹ፤”ሁከት የዘመናችን ዋነኛ መገበያያ ገንዘብ ሆኗል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ግራንዲ በአለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ተባብሶ በቀጠለው በየሃገሪቱ ባለዉ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች ክፉኛ ችግር ዉስጥ ይገኛሉም ብለዋል።
በተለይ ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች ከሱዳንና ዩክሬን የተፈናቀሉ መሆናቸዉንም ኮሚሺነሩ ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሺነሩ አክለዉም”በአጭርና በረጅም ጊዜ ደህንነታቸው የተጠበቀና አስተማማኝ ዋስትና እስካልተሰጣቸዉ ድርስ ተፈናቃዮችን ወደ ስፍራቸዉ መመለስ አይቻልም” ብለዋል ሲል የዘገበው የአፍሪካ ኒዉስ ።