የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ  ጭማሪ ተደረገ

Date:

የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሠረት፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 122 ብር ከ53 ሳንቲም
አንድ ሊትር ኬሮሲን 116 ብር ከ49 ሳንቲም
አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 116 ብር ከ49 ሳንቲም
አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 106 ብር ከ77 ሳንቲም
አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 104 ብር ከ08 ሳንቲም
አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109 ብር ከ56 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን የሚኒስቴር መ/ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም የቀላል ጥቁር ናፍጣ የሊትር መሸጫ ዋጋ 109 ብር 22 ሳንቲ የነበረ ሲሆን፤ የ3 ብር ከ55 ሳንቲም ቅናሽ ማሳየቱን ለማወቅ ተችሏል። አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106 ብር ከ75 ሳንቲም ከነበረበት ወደ 106 ብር ከ77 ሳንቲም ዝቅ ያለ ሲሆን፤ የአውሮፕላን ነዳጅም 113 ብር ከ20 ሳንቲም ከነበረበት ወደ 109 ብር ከ56 ሳንቲም መቀነሱ  ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...