የመንግስታቱ ድርጅት እንዳለው ጦርነቶችና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚጠፉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነዉ፡፡
ዓለምዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳስታወቀው በ 2024 ብቻ 56 ሺ ሰዎች ስለመጥፋታቸው ሪፖርት ደርሶታል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመካከለኛው ምስራቅ ረዳት ሴክሬታሪ ጄነራል ካሊድ ኪያሪ፤ይሄንን ችግር ለመፍታት የዓለምዓቀፍ ድጋፍና የዓለምዓቀፍ ህግ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በተለይም የሚጠፉ ሰዎች ቁጥር በፍልስጤሟ ጋዛና በዩክሬን ቁጥሩ ከፍ ማለቱንም ሃላፊው አንስተዋል፡፡
የሚጠፉ ሰዎችን በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት 2019 ላይ የጸደቀው ህግ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲሆንም ተጠይቋል፡፡
